የጀርባ ህመም ምልክቶች
Ethiopia - የጀርባ ክፍል (ወገብ) ህመም እንዴት ይከሰታል? መከላከያውስ? - የባለሙያ ምክር
የጀርባ ህመም ሲከሰት የተለያዩ ምልክቶች የሚኖሩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ እንደ የሰው ሁኔታና የበሽታ መከላከል ብቃት ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም የጀርባ ህመም ዋንኛ ምልክቶች እንደሆኑ ከሚታወቁት መካከል ራስ ምታት፣ የራስ ማዞርና መደንዘዝ፣ አንገት ለማዟዟር መቸገር፣ የእጅ መደንዘዝና እንደልብ አለመታዘዝ፣ ወገብ ላይ ቁርጥ የሚያደርግ ህመም መሰማት፣ የጡንቻዎች መወጣጠር ስሜት፣ ቁርጥማት፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ ሰገራና ሽንት መቆጣጠር አለመቻል፣ የእግርና የእጅ መሸማቀቅና እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር ህመም ይገኝበታል፡፡ ማንኛውም ሰው እነዚህን ምልክቶች በተደጋጋሚ ያስተዋለ እንደሆነ ወደ ባለሙያ ዘንድ በመሄድ ለችግሩ መፍትሔ መፈለግ ይኖርበታል፡፡
↧
The Doctor
↧